የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
ገላትያ 4:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን እላለሁ፤ ወራሹ ሕፃን ሳለ ለሁሉ ጌታ ሲሆን ከአገልጋይ የሚለይ አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ የምለው ይህ ነው፤ ወራሹ ሕፃን እስከ ሆነ ድረስ፣ ሀብት ሁሉ የርሱ ቢሆንም እንኳ፣ ከባሪያ የተለየ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንን እላለሁ፤ ወራሹ በሕፃንነት ዘመኑ ሁሉ፥ ምንም እንኳ የሁሉ ጌታ ቢሆንም ከባርያ አይለይም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም የምለው ይህን ነው፤ ወራሹ ሕፃን ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ምንም እንኳ የንብረቱ ሁሉ ጌታ ቢሆን ከባሪያ በምንም አይለይም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥ |
የንጉሡንም ልጅ አውጥቶ ዘውዱን ጫነበት፤ ምስክሩንም ሰጠው፤ ቀብቶም አነገሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይንገሥ” እያሉ በእጃቸው አጨበጨቡ።
ነገር ግን ከባሪያዪቱ የተወለደው ልደቱ ልዩ ነው፤ በሰው ልማድ ተወለደ፤ ከእመቤቲቱ የተወለደው ግን እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ ተወለደ።
በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።