ገላትያ 3:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃም በእግዚአብሔር እንደ አመነ፥ ጽድቅም ሆኖ እንደ ተቈጠረለት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልክ እንደዚሁ፣ አብርሃም “እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃም በእግዚአብሔር እንደ አመነና፥ ጽድቅም ሆኖ እንደ ተቆጠረለት፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም “አብርሃም በእግዚአብሔር አመነ፤ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ አብርሃም በእግዚአብሔር አመነና ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት። |
ስለ ኀጢአታችን የተሰቀለውን፥ ሊያስነሣንና ሊያጸድቀን የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ለይቶ በአስነሣው ስለምናምን ስለ እናም ነው እንጂ።