እንደ ተጻፈውም የዳስ በዓል አደረጉ፤ እንደ ሥርዐቱም ለየዕለቱ የተገባውን የየዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በቍጥር አቀረቡ።
ዘፀአት 5:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሠሪዎቹም፥ “ገለባ ትቀበሉበት እንደነበረ ጊዜ የቀን ሥራችሁን ጨርሱ” እያሉ ያስቸኩሉአቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባሪያ ተቈጣጣሪዎቹም “በየዕለቱ መሥራት የሚገባችሁ ሥራ ቀድሞ ጭድ ስናቀርብላችሁ ከምትሠሩት ሥራ ማነስ የለበትም” እያሉ ያጣድፏቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አስገባሪዎቹም፦ “ገለባ ትቀበሉበት እንደ ነበረ ጊዜ የቀን ሥራችሁን ጨርሱ” እያሉ አስቸኮሉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጨካኞች የሆኑትም አሠሪዎች ቀድሞ ገለባ እየሰጡአቸው ይሠሩት የነበረውን ያኽል ጡብ ቈጥረው እንዲያስረክቡ ያስገድዱአቸው ጀመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አስገባሪዎቹም፥ “ገለባ ትቀበሉበት እንደ ነበረ ጊዜ የቀን ሥራችሁን ጨርሱ፤” እያሉ አስቸኮሉአቸው። |
እንደ ተጻፈውም የዳስ በዓል አደረጉ፤ እንደ ሥርዐቱም ለየዕለቱ የተገባውን የየዕለቱን የሚቃጠል መሥዋዕት በቍጥር አቀረቡ።
በብርቱ ሥራም ያስጨንቋቸው ዘንድ የሠራተኞች አለቆችን ሾመባቸው፤ ለፈርዖንም ፌቶምን፥ ራምሴንና የፀሐይ ከተማ የምትባል ዖንን ጽኑ ከተሞች አድርገው ሠሩ።
የፈርዖንም ሹሞች፥ “ቀድሞ ታደርጉት እንደ ነበራችሁ እንደ ትናንትናውና እንደ ትናንትና በስቲያው የተቈጠረውን ጡብ ዛሬስ ስለምን አትጨርሱም?” እያሉ በእስራኤል ልጆች ላይ የተሾሙትን አለቆች ይገርፉ ነበር።