ለመሠዊያውም እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የናስ መከታ አድርግለት፤ ለመከታውም አራት የናስ ቀለበት በአራት ማዕዘኑ አድርግለት።
ዘፀአት 27:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ ይደርስ ዘንድ ከመሠዊያው እርከን በታች አኑረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ መሠዊያው ወገብ እንዲደርስ በመሠዊያው ዙሪያ ባለው እርከን ሥር አድርገው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ እንዲደርስ ከመሠዊያው እርከን በታች አድርገው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መከላከያም እስከ መሠዊያው እኩሌታ እንዲደርስ ከመሠዊያው ክፈፍ በታች አድርገው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከታውም እስከ መሠዊያው እኵሌታ ይደርስ ዘንድ መሰዊያው በሚዞረው በእርከኑ ታች አድርገው። |
ለመሠዊያውም እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የናስ መከታ አድርግለት፤ ለመከታውም አራት የናስ ቀለበት በአራት ማዕዘኑ አድርግለት።
ለመሠዊያውም ከማይነቅዝ ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርተህ በናስ ለብጣቸው፤ መሎጊያዎቹም በቀለበቶች ውስጥ ይግቡ፤
እንደ መረብ ሆኖም የተሠራ የናስ መከታ ለመሠዊያው አደረገ፤ መከታውም እስከ መሠዊያው እኩሌታ ይደርስ ዘንድ በመሠዊያው በሚዞረው በደረጃው ታች አደረገው።
በመሬቱም ላይ ከአለው መሠረት ጀምሮ እስከ ታችኛው እርከን ድረስ ሁለት ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ነው፤ ከትንሹም እርከን ጀምሮ እስከ ትልቁ እርከን ድረስ አራት ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ነው።