La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 26:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አምሳ ቀለ​በ​ቶ​ችን በአ​ንድ መጋ​ረጃ አድ​ርግ፤ አም​ሳ​ው​ንም ቀለ​በ​ቶች በሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ አድ​ርግ፤ ቀለ​በ​ቶቹ ሁሉ እርስ በር​ሳ​ቸው ፊት ለፊት ይሆ​ናሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቀለበቶችን ትይዩ በማድረግ ዐምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው ጠርዝ መጋረጃ፣ ዐምሳ ቀለበቶችንም በሌላው ጠርዝ መጋረጃ አድርግ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፥ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት እንዲሆኑ አድርግ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመጀመሪያው መጋረጃ መጀመሪያ ክፍል ላይ ኀምሳ ቀለበቶች፥ በሁለተኛው መጋረጃ መጨረሻ ክፍል ላይ ከሌሎቹ ቀለበቶች ፊት ለፊት ኀምሳ ቀለበቶች አድርግ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፥ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት ይሆናሉ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 26:5
3 Referencias Cruzadas  

ከሚ​ጋ​ጠ​ሙት መጋ​ረ​ጆች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ የሰ​ማ​ያ​ዊ​ውን ግምጃ ቀለ​በ​ቶች አድ​ርግ፤ ደግሞ ከተ​ጋ​ጠ​ሙት ከሌ​ሎች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ በውጭ በኩል እን​ዲሁ አድ​ርግ።


አምሳ የወ​ርቅ መያ​ዣ​ዎች ሥራ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን እርስ በር​ሳ​ቸው በመ​ያ​ዣ​ዎች አጋ​ጥ​ማ​ቸው፤ ድን​ኳ​ኑም አንድ ይሆ​ናል።


አምሳ ቀለ​በ​ቶ​ችን በአ​ንድ መጋ​ረጃ አደ​ረጉ፤ አም​ሳ​ው​ንም ቀለ​በ​ቶች በሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ አደ​ረጉ፤ ቀለ​በ​ቶቹ እርስ በር​ሳ​ቸው ፊት ለፊት የሚ​ተ​ያዩ ነበሩ።