“እውነተኛ ትውልድ እስክትነሣ ድረስ ትውልድ ከትውልድ ይልቅ አብልጣ ትበድላለችና በእነርሱ ላይ የተጻፈውን አየሁ፤ በደልም ትጠፋለች፤ ኀጢአትም ከምድር ላይ ትርቃለች፤ በጎውም ነገር ሁሉ በእርሷ ላይ ይመጣል፤ አሁንም ይህ የተወለደው ልጅ በእውነት የእርሱ ልጅ ነውና፥ ሐሰትም አይደለምና ሄደህ ለልጅህ ለላሜህ ንገረው፤” ማቱሳላም የአባቱ የሄኖክን ነገር በሰማ ጊዜ ሥራውን ሁሉ በስውር አሳይቶታልና ነገሩን ሰምቶ ተመለሰ።