“ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ የአንደኛውም ሰው ሚስት ባልዋን ከሚመታው ሰው እጅ ታድነው ዘንድ ብትቀርብ፥ እጅዋንም ዘርግታ ሁለቱን የብልቱን ፍሬዎች ብትይዝ፥
ዘዳግም 25:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤልም ዘንድ ስሙ ‘የጫማ ፈቱ ቤት’ ተብሎ ይጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዚያም ሰው የዘር ሐረግ በእስራኤል ዘንድ፣ “ጫማው የወለቀበት ቤት” ተብሎ ይታወቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚያም ሰው የዘር ሐረግ በእስራኤል ዘንድ፥ ‘ጫማው የወለቀበት ቤት’ ተብሎ ይታወቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዚያም ሰው ቤተሰብ በእስራኤል ‘ጫማው የወለቀበት ሰው ቤተሰብ’ እየተባለ በመነቀፍ ሲጠራ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤልም ዘንድ ስሙ የጫማ ፈቱ ቤት ተብሎ ይጠራ። |
“ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ የአንደኛውም ሰው ሚስት ባልዋን ከሚመታው ሰው እጅ ታድነው ዘንድ ብትቀርብ፥ እጅዋንም ዘርግታ ሁለቱን የብልቱን ፍሬዎች ብትይዝ፥
ዋርሳዪቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፦ ‘የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል’ ስትል የአንድ እግሩን ጫማ ታውጣ፤ በፊቱም እንትፍ ትበልበት።