ከእናንተ ከየነገዳችሁ ጥበበኞች፥ አስተዋዮችም፥ ዐዋቂዎችም የሆኑትን ሰዎች አምጡ፤ እኔም በላያችሁ አለቆች አደርጋቸዋለሁ።
ዘዳግም 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም፦ ‘እናደርገው ዘንድ የተናገርኸው ይህ ነገር መልካም ነው’ ብላችሁ መልሳችሁ ነገራችሁኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተም፣ “ይደረግ ዘንድ ያቀረብኸው ሐሳብ መልካም ነው” ብላችሁ መለሳችሁልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም፦ ‘እናደርገው ዘንድ የተናገርኸው ይህ ነገር መልካም ነው፥’ ብላችሁ መለሳችሁልኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተም ‘ያቀረብከው ሐሳብ መልካም ነው’ ብላችሁ መልስ ሰጥታችሁኝ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም፦ እናደርገው ዘንድ የተናገርኸው ይህ ነገር መልካም ነው ብላችሁ መለሳችሁልኝ። |
ከእናንተ ከየነገዳችሁ ጥበበኞች፥ አስተዋዮችም፥ ዐዋቂዎችም የሆኑትን ሰዎች አምጡ፤ እኔም በላያችሁ አለቆች አደርጋቸዋለሁ።
ከእናንተም ጥበበኞችና ዐዋቂዎች፥ አስተዋዮችም የሆኑትን ሰዎች ወሰድሁ፤ በእናንተም ላይ አለቆች፥ የሻለቆችም፥ የመቶ አለቆችም፥ የአምሳ አለቆችም፥ የዐሥር አለቆችም፥ ለፈራጆቻችሁም ጻፎች አድርጌ ሰየምኋቸው።