ከዚህ በኋላ የባቢሎን ሰዎች በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ፤ በንጉሡም ላይ ተነሡ፤ እንዲህም አሉ፥ “ንጉሥ ይሁዳዊ ሆነ፤ ቤልን ሰበረ፤ ካህናቱንም አረደ፤ ዘንዶውንም ገደለ።”