እርሱም፥ “እጅግ የተወደድህ ሰው ሆይ! አትፍራ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን፤ በርታ፤ ጽና፥” አለኝ። በተናገረኝም ጊዜ በረታሁና፥ “አበርትተኸኛልና ጌታዬ ይናገር” አልሁ።