La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 14:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህን ነገር እና​ገር ዘንድ እን​ድ​መጣ ይህን ምክር ያደ​ረገ አገ​ል​ጋ​ይህ ኢዮ​አብ ነው። ጌታዬ ግን በዚህ ዓለም የሚ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ታውቅ ዘንድ እንደ መል​አከ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ ጥበ​በኛ ነህ፤”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አገልጋይህ ኢዮአብ ይህን ያደረገውም ያለውን ሁኔታ ለመለወጥ ሲል ነው፤ ነገር ግን ጌታዬ የእግዚአብሔርን መልአክ ጥበብ የመሰለ ጥበብ ስላለው፣ በምድሪቱ ላይ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ያውቃል።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አገልጋይህ ኢዮአብ ይህን ያደረገውም የነገሩን መልክ ለመለወጥ ሲል ነው፤ ነገር ግን ጌታዬ ያለው ጥበብ የእግዚአብሔርን መልአክ ጥበብ ስለሚመስል፥ በምድሪቱ ላይ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ያውቃል።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱም ይህን ያደረገው ነገሮችን ሁሉ ለማስተካከል በማሰብ ነው፤ ንጉሥ ሆይ! አንተ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ጥበበኛ ነህ፤ የሚሆነውንም ነገር ሁሉ ታውቃለህ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባሪያህ ኢዮአብ የዚህ ነገር መልክ እንዲለውጥ አደረገ፥ ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ጠቢብ እንደ ሆነ፥ አንተም ጌታዬ በምድር ላይ ያለውን ነገር ሁሉ ታውቅ ዘንድ ጠቢብ ነህ አለች።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 14:20
12 Referencias Cruzadas  

ከእ​ር​ስዋ በበ​ላ​ችሁ ቀን፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ችሁ እን​ዲ​ከ​ፈቱ፥ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ም​ት​ሆኑ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን እን​ደ​ም​ታ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ​ሚ​ያ​ውቅ ነው እንጂ።”


ያችም ሴት አለች፥ “መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ውን ነገር ለመ​ስ​ማት ንጉሡ ጌታዬ እንደ መሥ​ዋ​ዕ​ትና እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነውና የጌ​ታዬ የን​ጉሡ ቃል እን​ደ​ዚሁ ነው፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ይሁን።”


እኔም በሰ​ው​ነቱ ላይ ክፉ ነገር ባደ​ርግ ነገሩ በን​ጉሡ ዘንድ ባል​ተ​ሰ​ወ​ረም ነበር፤ አን​ተም በተ​ነ​ሣ​ህ​ብኝ ነበር” አለው።


እር​ሱም በእኔ በባ​ሪ​ያህ ላይ ክፉ አደ​ረገ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ነህ፤ በፊ​ት​ህም ደስ ያሰ​ኘ​ህን አድ​ርግ።


የአ​ባቴ ቤት ሁሉ በጌ​ታዬ በን​ጉሥ ዘንድ ሞት የሚ​ገ​ባ​ቸው ነበሩ፤ አንተ ግን እኔን ባሪ​ያ​ህን በገ​በ​ታህ በሚ​በሉ መካ​ከል አስ​ቀ​መ​ጥ​ኸኝ፤ ለን​ጉሥ ደግሞ ለመ​ና​ገር ምን መብት አለኝ?”


ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠየቀ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በኋ​ላ​ቸው ዞረህ በሾ​ላው ዛፍ ፊት ለፊት ግጠ​ማ​ቸው እንጂ አት​ውጣ።


አን​ኩ​ስም መልሶ ዳዊ​ትን፥ “በዐ​ይኔ ፊት ጻድቅ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች፦ ‘ከእኛ ጋር ወደ ሰልፍ አይ​ወ​ጣም’ አሉ።