ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ለዳዊት ልጅ ለአቤሴሎም አንዲት የተዋበች እኅት ነበረችው፤ ስምዋም ትዕማር ነበረ፤ የዳዊትም ልጅ አምኖን ወደዳት።
2 ሳሙኤል 13:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምኖንም ከእኅቱ ከትዕማር የተነሣ እስከሚታመም ድረስ እጅግ ተከዘ፤ ድንግልም ነበረችና አንዳች ነገር ያደርግባት ዘንድ በዐይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖበት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምኖን እኅቱን ትዕማርን ከማፍቀሩ የተነሣ እስኪታመም ድረስ ተጨነቀ፤ ድንግል ስለ ሆነች እርሷን ማግኘት የማይቻል ሆኖ አግኝቶታልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኅቱን ትዕማርን ያፈቀረው አምኖን እስኪታመም ድረስ እጅግ ተሰቃየ፤ ድንግል ነበረችና አንዳች ነገር እንዳያደርግባት የማይታሰብ ሆኖበት አስጨነቀው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋንም እጅግ ከማፍቀሩ የተነሣ ታመመ፤ ድንግል ስለ ነበረች እርስዋን መገናኘት ከቶ አልተቻለውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምኖንም ከእኅቱ ከትዕማር የተነሣ እጅግ ስለ ተከዘ ታመመ፥ ድንግልም ነበረችና አንዳች ያደርጋት ዘንድ በዓይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖበት ነበር። |
ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ ለዳዊት ልጅ ለአቤሴሎም አንዲት የተዋበች እኅት ነበረችው፤ ስምዋም ትዕማር ነበረ፤ የዳዊትም ልጅ አምኖን ወደዳት።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ በምድረ በዳ ኀይልና ጽንዐት አምላችኋለሁ፤ ልጅ ወንድሜን ያገኛችሁት እንደ ሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ትነግሩት ዘንድ።
ስለ እግዚአብሔር ተብሎ የሚደረግ ኀዘን የዘለዓለም ሕይወትን የሚያሰጥ ንስሓ ነው። ስለ ዓለም የሚደረግ ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።