መቶ አለቆቹንና ኮራውያንን፥ ዘበኞችንና የሀገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰዳቸው፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወጣው፤ በዘበኞችም በር መንገድ ወደ ንጉሡ ቤት አመጡት፤ በነገሥታቱም ዙፋን አስቀመጡት።
2 ነገሥት 11:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሌላውም ከሦስት አንዱ እጅ በሰፊው መንገድ በበሩ በኩል ተቀመጡ፤ ሦስተኛውም እጅ ከዘበኞች ቤት በኋላ ባለው በር ሁኑ፤ ቤቱንም አጽንታችሁ ጠብቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሌላው ከሦስት እጅ አንዱ የሱርን በር ይጠብቅ፤ የቀረው ሌላው አንድ ሦስተኛው እጅ ደግሞ ቤተ መቅደሱን ተራ ገብቶ ከሚጠብቀው ከዘብ ጥበቃው ኋላ ያለውን በር ይጠብቅ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌላው አንድ ሦስተኛ እጅ የሱርን የቅጽር በር ይጠብቅ፤ የቀረው ሦስተኛ እጅ ደግሞ ከሌሎቹ ዘቦች በስተ ኋላ ያለውን ቅጽር በር ይጠብቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌላው አንድ ሦስተኛ እጅ የሱርን የቅጽር በር ይጠብቅ፤ የቀረው ሦስተኛ እጅ ደግሞ ከሌሎቹ ዘቦች በስተኋላ ያለውን ቅጽር በር ይጠብቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ በሱር በር ሁኑ፤ አንዱም እጅ ከዘበኞች ቤት በኋላ ባለው በር ሁኑ፤ ቤቱንም ጠብቁ፤ ከልክሉም፤ |
መቶ አለቆቹንና ኮራውያንን፥ ዘበኞችንና የሀገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰዳቸው፤ ንጉሡንም ከእግዚአብሔር ቤት አወጣው፤ በዘበኞችም በር መንገድ ወደ ንጉሡ ቤት አመጡት፤ በነገሥታቱም ዙፋን አስቀመጡት።
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እንዲህ አድርጉ፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ በበር ተቀምጣችሁ የንጉሡን ቤት ዘብ ጠብቁ፤