La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 2:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን ኢዮ​አብ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ኳን ሸሽቶ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀንድ እንደ ያዘ ሰማ፤ ንጉሥ ሰሎ​ሞ​ንም ወደ ኢዮ​አብ እን​ዲህ ሲል ላከ፤ “በመ​ሠ​ዊ​ያው ቀንድ የተ​ማ​ጠ​ንህ ምን ሆነህ ነው?” ኢዮ​አ​ብም፥ “ፈር​ቼ​ሃ​ለ​ሁና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ጠ​ንሁ” አለ። ሰሎ​ሞ​ንም የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን ልኮ፥ “ሂድ ግደ​ልና ቅበ​ረው” ብሎ አዘ​ዘው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መሆኑን ንጉሥ ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፣ የዮዳሄን ልጅ በናያስን፣ “ሂድና ግደለው!” ብሎ አዘዘው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢዮአብ ወደ ጌታ ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢዮአብ ወደ ተቀደሰ ድንኳን ሸሽቶ መሄዱንና በመሠዊያው አጠገብ መገኘቱን ሰሎሞን በሰማ ጊዜ፥ ኢዮአብን እንዲገድለው ለበናያ ትእዛዝ አስተላለፈ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ንጉሡም ሰሎሞን ኢዮአብ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን ሸሽቶ መሠዊያውን እንደ ያዘ ሰማ፤ ሰሎሞንም የዮዳሄን ልጅ በናያስን “ሂድ፤ ውደቅበት፤” ብሎ አዘዘው።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 2:29
9 Referencias Cruzadas  

የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያ​ስም አማ​ካሪ ነበረ፤ ከሊ​ታ​ው​ያ​ንና፥ ፊሊ​ታ​ው​ያን፥ የዳ​ዊ​ትም ልጆች የፍ​ርድ ቤት አለ​ቆች ነበሩ።


ንጉ​ሡም ሰሎ​ሞን የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በና​ያ​ስን ላከ፤ እር​ሱም አረ​ደው፤ ያን​ጊ​ዜም አዶ​ን​ያስ ሞተ።


የዮ​ዳሄ ልጅ በን​ያ​ስም ወደ ኢዮ​አብ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ኳን መጥቶ፥ “ንጉሡ፦ ውጣ ይል​ሃል” አለው፤ ኢዮ​አ​ብም፥ “በዚህ እሞ​ታ​ለሁ እንጂ አል​ወ​ጣም” አለ። የዮ​ዳሄ ልጅ በን​ያ​ስም፦ ተመ​ልሶ “ኢዮ​አብ የተ​ና​ገ​ረው ቃል፥ የመ​ለ​ሰ​ል​ኝም እን​ዲህ ነው” ብሎ ለን​ጉሡ ነገ​ረው።


ንጉ​ሡም አለው፥ “ሂድና እንደ ነገ​ረህ አድ​ርግ፤ ገድ​ለ​ህም ቅበ​ረው፤ ኢዮ​አ​ብም በከ​ንቱ ያፈ​ሰ​ሰ​ውን ደም ከእ​ኔና ከአ​ባቴ ቤት ታር​ቃ​ለህ።


ሰሎ​ሞ​ንም የዮ​ዳ​ሄን ልጅ በን​ያ​ስን አዘ​ዘው፤ ወጥ​ቶም ገደ​ለው። የሰ​ሎ​ሞ​ንም መን​ግ​ሥት በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ጸና።


ሰው ግን ቢሸ​ምቅ ጠላ​ቱ​ንም በተ​ን​ኰል ቢገ​ድ​ለ​ውና ቢማ​ፀን፥ እን​ዲ​ገ​ደል ከመ​ሠ​ዊ​ያዬ አው​ጥ​ተህ ውሰ​ደው።


ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንና ጎበ​ዙን፥ ድን​ግ​ሊ​ቱ​ንም፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንና ሴቶ​ቹን፥ ፈጽ​ማ​ችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምል​ክቱ ወደ አለ​በት ሰው ሁሉ አት​ቅ​ረቡ፤ በመ​ቅ​ደ​ሴም ጀምሩ” አላ​ቸው። በቤ​ቱም አን​ጻር ባሉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጀመሩ።


ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?