የዘለዓለም ቃል ኪዳንንም አጸናህለት፤ ልጆቹንም እስከ ዘለዓለም ፈጽመህ እንዳታጠፋቸው ተስፋ ሰጠኸው። ይስሐቅንም ሰጠኸው፤ ለይስሐቅም ያዕቆብንና ኤሳውን ሰጠኸው። ያዕቆብንም ለራስህ ለየህ፤ ኤሳውን ግን ጠላህ፤ ያዕቆብም ትልቅ ሕዝብ ሆነ፤