ምን አግዶኝ፥ በውጭ ባለው ላይ እፈርድበታለሁ? እናንተስ በውስጥ ከእናንተ ጋር የሚኖሩትን ፈርዳችሁ ቅጡአቸው።
1 ቆሮንቶስ 5:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ በሥጋዬ ከእናንተ ጋር ባልኖር፥ በመንፈሴ ከእናንተ ጋር አለሁ፤ እነሆ፥ ከእናንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠራውን እፈርድበታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንም እንኳ እኔ በአካል አብሬያችሁ ባልሆንም፣ በመንፈስ ግን ከእናንተ ጋራ ነኝ፤ ልክ አብሬያችሁ እንዳለሁ ሆኜ፣ ይህን ባደረገው ሰው ላይ አሁኑኑ ፈርጄበታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ከእናንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠራውን እፈርድበታለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም እንኳ እኔ በሥጋ አብሬአችሁ ባልሆን በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ልክ አብሬአችሁ እንዳለሁ ሆኜ እንዲህ ዐይነቱን ሥራ በፈጸመው ሰው ላይ በጌታ በኢየሱስ ስም ፈርጄበታለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥ |
ምን አግዶኝ፥ በውጭ ባለው ላይ እፈርድበታለሁ? እናንተስ በውስጥ ከእናንተ ጋር የሚኖሩትን ፈርዳችሁ ቅጡአቸው።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔ ጳውሎስ በእናንተ ዘንድ ፊት ለፊት ሳለሁ ትሑት የሆንሁ፥ ከእናንተ ብርቅ ግን የምደፍራችሁ በክርስቶስ የዋህነትና ቸርነት እማልዳችኋለሁ፥ በፍቅራችሁ እታመናለሁና።
ነገር ግን ይህን ነገር የሚናገር ይህን ይወቅ፤ በሌለንበት ጊዜ በመልእክታችን እንደ ተገለጠው እንደ ቃላችን፥ ባለንበትም ጊዜ በሥራችን እንዲሁ ነን።
ጥንቱን አስቀድሜ ተናግሬአለሁ፤ አሁንም አስቀድሜ እናገራለሁ፤ ቀድሞ ከእናንተ ጋር ሳለሁ እንደ ነገርሁአችሁ፥ አስቀድሞ ለበደሉ፥ ለሌሎችም ሁሉ እንደ ገና የመጣሁ እንደ ሆነ ርኅራኄ እንዳላደርግ፥ እንዲሁ ሳልኖር ለሦስተኛ ጊዜ እናገራለሁ፥
እኔ በሥጋ ከእናንተ ዘንድ ባልኖርም እንኳን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባያችሁንና ሥርዐታችሁን፥ በክርስቶስም ያለ የእምነታችሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለኛል።