1 ቆሮንቶስ 14:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተቀምጦ ሳለ ምሥጢር የተገለጠለት ቢኖር ፊተኛው ዝም ይበል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተቀመጡትም መካከል አንድ ሰው አንድ ነገር ቢገለጥለት፣ የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተቀመጡትም መካከል አንድ ሰው አንድ ነገር ቢገለጥለት፥ የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስብሰባ ላይ ለሚገኝ ሌላ ሰው አንዳች ራእይ ቢገለጥለት፤ የመጀመሪያው ተናጋሪ ዝም ይበል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ለሚቀመጥ ለሌላ ግን አንድ ነገር ቢገለጥለት ፊተኛው ዝም ይበል። |
አሁንም ወንድሞቻችን ሆይ፥ ሁላችሁ በምትሰበሰቡበት ጊዜ መዝሙር አላችሁ፤ ትምህርት አላችሁ፤ መግለጥ አላችሁ፤ በቋንቋ መናገር አላችሁ፤ መተርጐምም አላችሁ፤ ሁሉም ለሚታነጽበት ጥቅም አድርጉት።
አሁንም ወንድሞች ሆይ፥ ወደ እናንተ መጥቼ በማታውቁት ቋንቋ ባነጋግራችሁ፥ የጥበብ ነገርንም ቢሆን፥ የትንቢትንም ነገር ቢሆን፥ የማስተማር ሥራንም ቢሆን ገልጬ ካልነገርኋችሁ የምጠቅማችሁ ጥቅም ምንድን ነው?