Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 14:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ሁሉ እን​ዲ​ማር፥ ሁሉም ደስ እን​ዲ​ለው፥ እን​ዲ​ጸ​ናም ሁላ​ችሁ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ትን​ቢት ልት​ና​ገሩ ትች​ላ​ላ​ች​ሁና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 እያንዳንዳችሁ እንድትማሩና እያንዳንዳችሁ እንድትበረታቱ፣ ሁላችሁ በየተራ ትንቢት መናገር ትችላላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 እያንዳንዳችሁ እንድትማሩና እያንዳንዳችሁ እንድትበረታቱ፥ ሁላችሁ በየተራ ትንቢት መናገር ትችላላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 እያንዳንዱ እንዲማርና እንዲጽናና ሁላችሁም በየተራ የእግዚአብሔርን መልእክት መናገር ትችላላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ሁሉም እንዲማሩ ሁሉም እንዲመከሩ ሁላችሁ በእያንዳንዳችሁ ትንቢት ልትናገሩ ትችላላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 14:31
17 Referencias Cruzadas  

ጠቢብ እነዚህን በመስማት ጥበብን ይጨምራል፥ አስተዋይ ግን ምክርን ገንዘብ ያደርጋል።


ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጻድቅንም አስተምረው፥ ዕውቀትንም ያበዛል።


ይህ​ንም ማለቴ በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ባለች በእ​ና​ን​ተና በእኔ እም​ነት አብ​ረን በእ​ና​ንተ እን​ድ​ን​ጽ​ናና ነው።


ነገር ግን ሌሎ​ችን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በቋ​ንቋ ከሚ​ነ​ገር ብዙ ቃል ይልቅ በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን በአ​እ​ም​ሮዬ አም​ስት ቃላ​ትን ልና​ገር እሻ​ለሁ።


ትን​ቢ​ትን የሚ​ና​ገር ግን ለማ​ነ​ጽና ለመ​ም​ከር፥ ለማ​ረ​ጋ​ጋ​ትም ለሰው ይና​ገ​ራል።


ተቀ​ምጦ ሳለ ምሥ​ጢር የተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ቢኖር ፊተ​ኛው ዝም ይበል።


የነ​ቢ​ያት ሀብት ለነ​ቢ​ያት ይሰ​ጣ​ልና።


ለሴት በቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን መና​ገር ክል​ክል ነው፤ ሊማሩ ከወ​ደዱ ደግሞ በቤ​ታ​ቸው ባሎ​ቻ​ቸ​ውን ይጠ​ይቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ጽ​ና​ናን በዚያ መጽ​ና​ናት በመ​ከራ ያሉ​ትን ሁሉ ማጽ​ና​ናት እን​ችል ዘንድ ከመ​ከ​ራ​ችን ሁሉ ያጽ​ና​ናን እርሱ ይመ​ስ​ገን።


ዜና​ዬን ታውቁ ዘንድ፥ ልባ​ች​ሁም ይጽ​ናና ዘንድ፥ ስለ​ዚህ ወደ እና​ንተ ላክ​ሁት።


ይኸ​ውም ልቡ​ና​ቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትም​ህ​ር​ታ​ቸ​ውም በማ​ወቅ፥ በፍ​ቅ​ርና ፍጹ​ም​ነት ባለው ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በጥ​በ​ብና በሃ​ይ​ማ​ኖት፥ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም የሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር በማ​ወቅ ይጸና ዘንድ ነው።


ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።


ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ፥ እርስ በርሳችሁ ተመካከሩ፤ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው።


ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።


ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos