የቋንቋውን ትርጓሜ ካላወቅሁ እኔ ለሚያነጋግረኝ እንደ እንግዳ እሆንበታለሁ፤ የሚያነጋግረኝ እርሱም ለእኔ እንደ እንግዳ ይሆናል።
1 ቆሮንቶስ 14:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዓለም ልዩ ልዩ ቋንቋዎች አሉ፤ ከእነርሱም ትርጕም የሌለው አንድም የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዓለም ላይ ብዙ ዐይነት ቋንቋዎች አሉ፤ ትርጕም የሌለውም ቋንቋ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዓለም ላይ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎች አሉ፤ ትርጒም የሌለውም ቋንቋ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዓለም ላይ ብዙ ቋንቋዎች አሉ፤ ትርጒም የሌለው ቋንቋም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዓለም ምናልባት ቁጥር የሌለው የቋንቋ ዓይነት ይኖራል ቋንቋም የሌለው ሕዝብ የለም፤ |
የቋንቋውን ትርጓሜ ካላወቅሁ እኔ ለሚያነጋግረኝ እንደ እንግዳ እሆንበታለሁ፤ የሚያነጋግረኝ እርሱም ለእኔ እንደ እንግዳ ይሆናል።
እንዲሁም እናንተ በማይታወቅ ቋንቋ ብትናገሩ፥ ይህንኑም ገልጣችሁ ባትተረጕሙ የምትሉትንና የምትናገሩትን ማን ያውቃል? ከነፋስ ጋር እንደምትነጋገሩ ትሆናላችሁ።