1 ቆሮንቶስ 14:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 እንዲሁም እናንተ በማይታወቅ ቋንቋ ብትናገሩ፥ ይህንኑም ገልጣችሁ ባትተረጕሙ የምትሉትንና የምትናገሩትን ማን ያውቃል? ከነፋስ ጋር እንደምትነጋገሩ ትሆናላችሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 እናንተም እንደዚሁ ናችሁ፤ ከአንደበታችሁ ትርጕም ያለው ቃል ካልወጣ፣ የምትናገሩትን ማን ሊያስተውለው ይችላል? ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 እናንተም እንደዚሁ ናችሁ፤ ከአንደበታችሁ የሚታወቅ ቃል ካልወጣ፥ የምትናገሩትን ማን ሊያስተውለው ይችላል? ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እንዲሁም እናንተ በቋንቋ ስትነጋገሩ ግልጥ በሆኑ ቃሎች ካልተናገራችሁ የምትናገሩትን ማን ሊያውቀው ይችላል? ለነፋስ እንደምትናገሩ ትሆናላችሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የተገለጠውን ቃል በአንደበት ባትናገሩ ሰዎች የምትናገሩትን እንዴት አድርገው ያስተውሉታል? ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁና። Ver Capítulo |