1 ዜና መዋዕል 7:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሹቱላ፥ ልጁ ኤድር፥ ልጁ ኤልዓድ ነበሩ፤ የሀገሩም ተወላጆች የጌት ሰዎች ከብቶቻቸውን ሊወስዱ ወርደው ነበርና ገደሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጁ ዛባድ፣ ልጁ ሹቱላ። ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣ የአገሩ ተወላጆች በሆኑት በጋት ሰዎች ተገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሹቱላ፥ የአገሩም ተወላጆች የጌት ሰዎች ከብቶቻቸውን ሊወስዱ ወርደው ነበርና የገደሉአቸው ልጆቹ ኤድርና ኤልዓድ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታሐት ዛባድን ወለደ፤ ዛባድ ሹቴላሕን ወለደ፤ ኤፍሬም ከሹቴላሕ ሌላ ዔዜርና ኤልዓድ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም የጋት ነዋሪዎችን የቀንድ ከብቶች ሲሰርቁ ተይዘው ተገደሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጁ ዛባድ፥ ልጁ ሹቱላ፥ የአገሩም ተወላጆች የጌት ሰዎች ከብቶቻቸውን ሊወስዱ ወርደው ነበርና የገደሉአቸው ልጆቹ ኤድርና ኤልዓድ ነበሩ። |
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ፍልስጥኤማውያን በቀልን አድርገዋልና፥ በቀላቸውንም አጽንተዋልና፥ እስራኤልም ለዘለዓለም ይጠፉ ዘንድ ነፍሳቸው ደስ ይላታልና፤
የእግዚአብሔርንም ታቦት ወደ አስቀሎና ላኩአት። የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አስቀሎና በመጣች ጊዜ አስቀሎናውያን፥ “እኛንና ሕዝባችንን ልታስገድሉን የእስራኤልን አምላክ ታቦት ለምን አመጣችሁብን?” ብለው ጮኹ።
ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ወደ እነርሱ ሰበሰቡና፥ “በእስራኤል አምላክ ታቦት ምን እናድርግ?” አሉ፤ የጌት ሰዎችም፥ “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ እኛ ትዙር” ብለው መለሱ። የእስራኤል አምላክ ታቦትም ወደ ጌት ሄደች።