ደግሞም የምድሜናን አባት ስጋብን የመክቢናንና የጌባልን አባት ሳዑልን ወለደች፤ የካሌብም ሴት ልጅ አስካ ነበረች።
1 ዜና መዋዕል 2:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካሌብም ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ የኤፍራታ የበኵሩ የኦር ልጅ የቀርያታርም አባት ሶባል ነበር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሁሉ የካሌብ ዘሮች ነበሩ። የኤፍራታ የበኵር ልጅ የሑር ወንዶች ልጆች፤ ሦባል የቂርያትይዓይሪም አባት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካሌብ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የኤፍራታ የበኩሩ የሆር ልጅ የቂርያት-ይዓሪም አባት ሦባል፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ የሚከተሉትም የካሌብ ዘሮች ናቸው፦ ሑር የካሌብ ከሚስቱ ከኤፍራታ የተወለደው የመጀመሪያው ልጁ ሲሆን የሑር ልጅ የቂርያትይዓሪም አባት ሾባል ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካሌብ ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የኤፍራታ የበኵሩ የሆር ልጅ የቂርያትይዓሪም አባት ሦባል፥ |
ደግሞም የምድሜናን አባት ስጋብን የመክቢናንና የጌባልን አባት ሳዑልን ወለደች፤ የካሌብም ሴት ልጅ አስካ ነበረች።
የቀርያታርም ወገኖች፤ ይትራውያን፥ ፋታውያን፥ ሹማታውያን፥ ሚሸራውያን፤ ከእነዚህም ሶራሐውያንና ኤሽታአላውያን ወጡ።
ቴቆ፥ ኤፍራታ፥ ይኽችውም ቤተ ልሔም ናት፤ ፋጎርም፥ ኤጣንም፥ ቁሎን፥ ጠጦንም፥ ሶብሄም፥ ቃሬም፥ ጌሌም፥ ኤቴር፥ መነኮም፥ ዐሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው፥ ቅርያትበኣል፥ ይኽችውም የኢያርም ከተማ ናት፤ ሶቤታ፥ ሁለቱ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄዳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ይደርሳል፤ ወደ ኢያሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደርሳል።
የእስራኤልም ልጆች ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮትና ኢያሪም ነበሩ።
በከተማይቱ በር አደባባይም የነበሩ ሕዝብ ሁሉ ሽማግሌዎቹም፦ እኛ ምስክሮች ነን፣ እግዚአብሔር ይህችን ወደ ቤትህ የምትገባውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ሠሩ እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርጋት፣ አንተም በኤፍራታ ባለ ጠጋ ሁን፥ ስምህም በቤተ ልሔም ይጠራ።
የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡአት፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።