La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 13:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዖዛ ላይ ተቈጣ። እጁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ስለ ዘረጋ ቀሠ​ፈው፤ በዚ​ያም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞተ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ታቦቱን በእጁ ስለ ነካ፣ የእግዚአብሔር ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ ስለዚህም በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጌታም ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፥ እጁንም ወደ ታቦቱ ስለዘረጋ ቀሠፈው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዑዛ ታቦቱን በመንካቱ እግዚአብሔር ተቈጥቶ ወዲያውኑ በሞት ቀሠፈው፤ ስለዚህም ዑዛ በዚያው በእግዚአብሔር ፊት ሞተ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ እጁንም ወደ ታቦቱ ስለዘረጋ ቀሠፈው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 13:10
10 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዖዛን ስለ ሰበ​ረው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚ​ያን ስፍራ ስም “የዖዛ ስብ​ራት” ብሎ ጠራው።


በቀ​ድሞ ሥራ​ችን አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርስ በር​ሳ​ችን አላ​ጠ​ፋ​ንም፤ በጦ​ር አል​ፈ​ለ​ገ​ን​ምና” አላ​ቸው።


በመ​ጽ​ሐ​ፍም እንደ ተጻፈ ሙሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ አዘ​ዛ​ቸው የሌ​ዋ​ው​ያን ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት በት​ከ​ሻ​ቸው ላይ በመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎቹ ተሸ​ከሙ። መባ​እና ቍር​ባ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ።


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥታ ያጥኑ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች በላች።


አሮ​ንና ልጆቹ መቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ ሁሉ ሸፍ​ነው ከጨ​ረሱ በኋላ ሰፈሩ ሲነሣ የቀ​ዓት ልጆች ሊሸ​ከ​ሙት ይገ​ባሉ። እን​ዳ​ይ​ሞቱ ግን ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን አይ​ንኩ። በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዘንድ የቀ​ዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ከሙ፤ ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት ወስ​ደው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላ​ቸው።


የኢ​ያ​ኮ​ንዩ ልጆ​ችም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ተመ​ል​ክ​ተው ከቤ​ት​ሳ​ሚስ ሰዎች ጋር አል​ተ​ቀ​በ​ሉ​አ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሕ​ዝቡ አም​ስት ሺህ ሰባ ሰዎ​ችን መታ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕዝ​ቡን በታ​ላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለ​ቀሱ።