ሶፎንያስ 2:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀርጤስ ሰዎች የሚኖሩበት በባሕሩ ዳር ያለው ምድር፣ የእረኞች መኖሪያና የበጎች በረት ይሆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባሕሩም ዳር የግጦሽ መሬት፥ የእረኞች መስክና የበጎች በረት ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባሕር ዳር ያለው ምድራችሁ የከብት ማሰማሪያ፥ የእረኞች መኖሪያና የመንጋዎች ማደሪያ በረት ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀርጤስም የእረኞች መኖሪያና የመንጎች በረት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀርጤስም የእረኞች መኖሪያና የመንጎች በረት ይሆናል። |
ኵርንችትና እሾኹን በመፍራት ከዚህ በፊት በመቈፈሪያ ተቈፍረው ወደ ነበሩት ወደ እነዚያ ኰረብቶች ሁሉ ከእንግዲህ አትሄድም፤ ነገር ግን የከብቶች መሰማሪያና የበጎች መፈንጫ ቦታ ይሆናሉ።
“የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሰውም ሆነ እንስሳት በማይኖሩበት በዚህ ባዶ ስፍራ፣ በከተማዎቹም ሁሉ እረኞች መንጎቻቸውን የሚያሳርፉበት እንደ ገና ያገኛሉ።