መዝሙር 97:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ፍርድህ፣ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፤ የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ስለ ትክክለኛ ፍርድህ የጽዮን ሕዝብ ደስ ይላቸዋል፤ የይሁዳ ከተሞችም ሐሤት ያደርጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዞችም በአንድነት በእጅ ያጨብጭቡ፥ ተራሮች ደስ ይበላቸው፥ |
እግዚአብሔር ጽዮንን በርግጥ ያጽናናታል፤ ፍርስራሾቿንም በርኅራኄ ይመለከታል፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔድን፣ በረሓዋንም እንደ እግዚአብሔር ተክል ቦታ ያደርጋል፤ ተድላና ደስታ፣ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ በርሷ ይገኛሉ።
እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ፣ እንዲህ ሲል ዐውጇል፤ “ለጽዮን ሴት ልጅ፣ ‘እነሆ፤ አዳኝሽ መጥቷል! ዋጋሽ በእጁ አለ፤ ዕድል ፈንታሽም ከርሱ ጋራ ነው’ በሏት።”
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።
“ሰማይ ሆይ፤ በርሷ ላይ ሐሤት አድርግ! ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያትም ሐሤት አድርጉ! በእናንተ ላይ ባደረሰችው ነገር እግዚአብሔር ፈርዶባታልና።”