መዝሙር 26:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሕረትህ ከፊቴ አልተለየምና፣ በእውነትህም ተመላለስሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቸርነትህ በዓይኔ ፊት ነውና፥ በእውነትህም ተመላለስሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የማያቋርጠው ፍቅርህ በዐይኖቼ ፊት ነው፤ ዘወትር የሚመራኝም የአንተ ታማኝነት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሠራዊትም ቢጠላኝ ልቤ አይፈራብኝም፤ ሠራዊትም ቢከቡኝ በእርሱ እተማመናለሁ። |
እኛም ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያንጸባረቅን፣ የርሱን መልክ እንድንመስል ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን፤ ይህም የሚሆነው መንፈስ ከሆነ ጌታ ነው።
የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና፤ በርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ሀብታም ሆኖ ሳለ ለእናንተ ሲል ድኻ ሆነ።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ እኛም በብርሃን ብንመላለስ፣ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፤ የልጁም የኢየሱስ ደም ከኀጢአት ሁሉ ያነጻናል።
ወዳጅ ሆይ፤ መልካም የሆነውን እንጂ ክፉውን አትምሰል። መልካም የሆነውን የሚያደርግ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው። ክፉ የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።