ምሳሌ 8:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የርሱ በሆነው መላው ዓለም ሐሤት እያደረግሁ፣ በሰው ልጆች ደስ እሰኝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደስታዬም በምድሩ ተድላዬም በሰው ልጆች ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በፈጠረው ዓለም ደስ ይለኛል፤ በሰው ዘርም ሐሤት አደርጋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓለምንም ፈጥሮ በፈጸመና ደስ ባለው ጊዜ፥ ደስታዬ በሰው ልጆች መካከል ነበር። |
ጊዜው ልክ ከፋሲካ በዓል በፊት ነበረ፤ ኢየሱስም ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዐወቀ። በዓለም የነበሩትን፣ የራሱ የሆኑትን ወደዳቸው፤ በፍጹም ፍቅሩም ወደዳቸው።
የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና፤ በርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ሀብታም ሆኖ ሳለ ለእናንተ ሲል ድኻ ሆነ።