ምሳሌ 18:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለክፉ ሰው ማድላት፣ ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ፍርድ ይጠምም ዘንድ፥ ለኀጥእም ማድላት መልካም አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለበደለኛው ማዳላትና ንጹሕ ሰው ትክክለኛ ፍትሕ እንዳያገኝ ማድረግ ተገቢ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም። በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥ |
እጆቹ ክፉ ለማድረግ ሠልጥነዋል፤ ገዥው እጅ መንሻ ይፈልጋል፤ ፈራጁ ጕቦ ይቀበላል፤ ኀይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ፤ ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ።
ደቀ መዛሙርታቸውን ከሄሮድስ ወገኖች ጋራ ወደ እርሱ ልከው እንዲህ አሉት፤ “መምህር ሆይ፤ አንተ እውነተኛና የእግዚአብሔርንም መንገድ በእውነት የምታስተምር እንደ ሆንህ፣ ለማንም ሳታደላ ሁሉን እኩል እንደምትመለከት እናውቃለን፤