Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 18:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤ የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የሰው አፍ ቃል የጠለቀ ውኃ ነው፥ የጥበብም ምንጭ ፈሳሽ ወንዝ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከሰው አንደበት የሚወጣው የጥበብ ንግግር እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤ እንደ ምንጭ ውሃም ጣፋጭ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ቃል በብልህ ሰው ልብ ውስጥ የጠለቀ ውኃ ነው፥ የሚፈልቅም የሕይወት ምንጭና ፈሳሽ ወንዝ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 18:4
11 Referencias Cruzadas  

የሰው ልብ ሐሳብ እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤ አስተዋይ ሰው ግን ከዚያ ቀድቶ ያወጣዋል።


የጻድቅ አንደበት የሕይወት ምንጭ ናት፤ መዓት ግን የክፉዎችን አፍ ይዘጋል።


ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ በጨው እንደ ተቀመመ ሁልጊዜ በጸጋ የተሞላ ይሁን።


እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ግን ከቶ አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል።”


የጠቢብ ትምህርት የሕይወት ምንጭ ናት፤ ሰውን ከሞት ወጥመድ ያድነዋል።


የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በጥበብ ሁሉ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በማሕሌት፣ በመንፈሳዊም ቅኔ በማመስገን በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።


እናንተ የእፉኝት ልጆች፤ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ መልካም ነገር መናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ የሞላውን አንደበት ይናገረዋልና።


አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከጥንት በነበረ እንቈቅልሽ እናገራለሁ፤


ማስተዋልን ገንዘብ ላደረጋት የሕይወት ምንጭ ናት፤ ቂልነት ግን በቂሎች ላይ ቅጣት ታመጣባቸዋለች።


ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤ ከዕፍረትም ጋራ ውርደት ትመጣለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios