La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 13:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ያላግባብ የተገኘ ገንዘብ እየተመናመነ ያልቃል፤ ገንዘቡን ጥቂት በጥቂት የሚያከማች ግን ይጠራቀምለታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በችኰላ የምትከማች ሀብት ትጐድላለች፥ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያለ ድካም በቀላሉ የተገኘ ሀብት ወዲያው ይጠፋል፤ ተግቶ በመሥራት የተገኘ ሀብት ግን እየበዛ ይሄዳል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በኀጢአት በችኮላ የሚገኝ ሀብት ይጐድላል፥ በእውነት ለራሱ የሚሰበስብ ግን ይበዛለታል። ጻድቅ ይራራል፥ ያበድራልም።

Ver Capítulo



ምሳሌ 13:11
19 Referencias Cruzadas  

የዋጠውን ሀብት ይተፋል፤ እግዚአብሔርም መልሶ ከሆዱ ያወጣዋል።


የድካምህን ፍሬ ትበላለህ፤ ብፅዕና እና ብልጽግና የአንተ ይሆናሉ።


ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።


ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፤ ጥበብ ግን ምክርን በሚቀበሉ ዘንድ ትገኛለች።


ለነገ የሚባል ተስፋ ልብን ያሳምማል፤ የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው።


ከጅምሩ ወዲያው የተገኘ ርስት፣ በመጨረሻ በረከት አይኖረውም።


በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣ በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው።


ታማኝ ሰው እጅግ ይባረካል፤ ሀብት ለማግኘት የሚጣደፍ ግን ከቅጣት አያመልጥም።


ስስታም ሀብት ለማከማቸት ይስገበገባል፤ ድኽነት እንደሚጠብቀውም አያውቅም።


በከፍተኛ ወለድ ሀብቱን የሚያካብት፣ ለድኻ ለሚራራ፣ ለሌላው ሰው ያከማችለታል።


ወይም በአንድ መጥፎ አጋጣሚ የጠፋ ብልጽግና ነው፤ ልጅ ሲወልድም፣ ለርሱ የሚያስቀርለት ምንም ነገር አይኖርም።


ሀብትን በግፍ የሚያከማች ሰው፣ ያልፈለፈለችውን ጫጩት እንደምትታቀፍ ቆቅ ነው፤ በዕድሜው አጋማሽ ትቶት ይሄዳል፤ በመጨረሻም ሞኝነቱ ይረጋገጣል።