ምሳሌ 1:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ በየዐይነቱ እናገኛለን፤ ቤቶቻችንንም በዝርፊያ እንሞላለን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካምና ውድ ሀብት ሁሉ እናገኛለን፥ ከምርኮውም ቤታችንን እንሞላለን፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውድ የሆኑ ብዙ ዐይነት ዕቃዎች እናገኛለን፤ ከቅሚያ በተገኘ ሀብት ቤቶቻችንን እንሞላለን፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ሀብቱን እንሰብስብ፥ ከምርኮውም ቤታችንን እንሙላ፤ |
ለአዛጦን ምሽግ፣ ለግብጽም ምሽግ እንዲህ ብላችሁ ዐውጁ፤ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤ በውስጧ ያለውን ታላቅ ሁከት፣ በሕዝቧም መካከል ያለውን ግፍ እዩ።”
‘የዚህ የአሁኑ ቤት ክብር ከቀድሞው ቤት ክብር ይበልጣል’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ‘በዚህም ቦታ ሰላምን እሰጣለሁ’ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”