ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺሕ በሬ፣ መቶ ሃያ ሺሕ በግና ፍየል የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ንጉሡና እስራኤላውያንም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በዚህ ሁኔታ ቀደሱ።
ዘኍል 7:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የሶገር ልጅ ናትናኤል ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንድነትም መሥዋዕት ሁለት በሬዎች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቀረበ፤ የሶገር ልጅ የናትናኤ መባ ይህ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች አቀረበ፤ የሰገር ልጅ የናትናኤል መባ ይህ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት በሬዎች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦቶች አቀረበ፤ የሶገር ልጅ የናትናኤ መባ ይህ ነበረ። |
ሰሎሞንም ሃያ ሁለት ሺሕ በሬ፣ መቶ ሃያ ሺሕ በግና ፍየል የኅብረት መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ንጉሡና እስራኤላውያንም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በዚህ ሁኔታ ቀደሱ።