ዘኍል 17:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ለእስራኤላውያን ተናገራቸው፤ አለቆቻቸውም በቀደሙት በእያንዳንዱ አባቶች ስም ዐሥራ ሁለት በትር ሰጡት፤ የአሮን በትርም በበትሮቹ መካከል ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገረ፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዐሥራ ሁለት በትሮች፥ እያንዳንዱም አለቃ በየአባቱ ቤት አንድ አንድ በትር፥ ሰጡት፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሙሴ ይህንኑ ለእስራኤላውያን ነገራቸው፤ እያንዳንዱም መሪ በትሩን አምጥቶ ሰጠው፤ ስለያንዳንዱ የነገድ መሪ የሚሰጠው አንዳንድ በትር ሆኖ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት በትሮች ቀረቡ፤ ከእነዚያም በትሮች መካከል የአሮን በትር ነበረች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ነገራቸው፤ አለቆቻቸውም ሁሉ አንድ አንድ በትር ሰጡት፤ ለአንድ አለቃ አንድ በትር፥ በየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገራቸው፤ አለቆቻቸው ሁሉ አሥራ ሁለት በትሮች፥ እያንዳንዱም አለቃ በየአባቱ ቤት አንድ አንድ በትር፥ ሰጡት፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች። |
እስራኤላውያን በሙሉ በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ፤ ማኅበሩም ሁሉ እንዲህ አሏቸው፤ “ምነው በግብጽ ወይም በዚህ ምድረ በዳ ሞተን ባረፍነው ኖሮ!
ብቻ በእግዚአብሔር ላይ አታምፁ፤ እንደ እንጀራ እንጐርሳቸዋለንና የምድሪቱን ሰዎች አትፍሯቸው። ጥላቸው ተገፍፏል፤ እግዚአብሔርም ከእኛ ጋራ ነውና አትፍሯቸው።”