ዘኍል 10:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም የሮቤል ሰፈር ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ሆነው ተጓዙ፤ አለቃቸውም የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሮቤልም ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር አለቃ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም በሮቤል ነገድ ቡድን ሰንደቅ ዓላማ ሥር የሚገኙት በሸዴኡር ልጅ በኤሊጹር መሪነት የቡድን ተራቸውን ጠብቀው ተጓዙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሮቤልም ሰፈር በሥርዐታቸው ከየሠራዊቶቻቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር አለቃ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሮቤልም ሰፈር ዓላማ በየሠራዊታቸው ተጓዘ፤ በሠራዊቱም ላይ የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር አለቃ ነበረ። |
እንዲሁም ለኅብረት መሥዋዕት የሚቀርብ ሁለት በሬ፣ ዐምስት አውራ በግ፣ ዐምስት ተባዕት ፍየል እንዲሁም አንድ ዓመት የሆናቸው ዐምስት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ነበሩ። እንግዲህ የስዲዮር ልጅ ኤሊሱር ያቀረበው ስጦታ ይህ ነበር።