ማቴዎስ 4:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አርባ ቀን እና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። |
ሙሴ እህል ሳይበላ፣ ውሃም ሳይጠጣ ከእግዚአብሔር ጋራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በዚያ ነበር፤ በጽላቱ ላይ የቃል ኪዳኑን ቃሎች፣ ዐሥርቱ ትእዛዛትን ጻፈ።
በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጕድጓድ ነበረ፤ ኢየሱስም ከጕዞው የተነሣ ደክሞት ስለ ነበር በውሃው ጕድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ነበር።
ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን በመፈጸም ለቍጣ እንዲነሣሣ የሚያደርገውን ኀጢአት ሁሉ ስለ ሠራችሁ፣ እህል ውሃ ሳልቀምስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እንደ ገና በእግዚአብሔር ፊት በግንባሬ ተደፋሁ።
እኔም የድንጋይ ጽላቱን፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ የገባውን የኪዳን ጽላት ለመቀበል ወደ ተራራው በወጣሁ ጊዜ፣ እህል ሳልበላ፣ ውሃም ሳልጠጣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየሁ፤