ማቴዎስ 23:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ የአባቶቻችሁን ጅምር ተግባር ከፍጻሜ አድርሱ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ፈጽሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲያውስ አባቶቻችሁ የጀመሩትን እናንተም ፈጽሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ደግሞ የአባቶቻችሁን መስፈሪያ ሙሉ። |
ፍቅርና ቸርነትን ለእልፍ አእላፍ ታሳያለህ፤ ይሁን እንጂ የአባቶችን በደል ከእነርሱ በኋላ በሚነሡ ልጆቻቸው ጕያ ትመልሳለህ፤ ስምህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ፣ ታላቅና ኀያል አምላክ ሆይ፤
ይኸውም ይድኑ ዘንድ ለአሕዛብ እንዳንናገር ለመከልከል ነው፤ በዚህ ሁኔታ ኀጢአታቸውን ሁልጊዜ በራሳቸው ላይ እስከ መጨረሻው እያከማቹ ይሄዳሉ። ቍጣውም በእነርሱ ላይ ያለ ልክ መጥቷል።