Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 32:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “እናንተ የኀጢአተኞች ልጆች ይኸው በአባቶቻችሁ እግር ተተክታችሁ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ይበልጥ እንዲቈጣ ታደርጋላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እነሆም፥ የጌታን መዓት በእስራኤል ላይ አብዝታችሁ ለመጨመር እናንተ የኃጢአተኞች ትውልድ በአባቶቻችሁ ፋንታ ተነሣችሁ!

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አሁን ደግሞ እናንተ በአባቶቻችሁ ስፍራ ተተክታችኋል፤ የእግዚአብሔርንም ቊጣ በእስራኤል ላይ ለማምጣት የተዘጋጀ አዲስ ኃጢአተኛ ትውልድ ሆናችኋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መዓት በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አብ​ዝ​ታ​ችሁ ትጨ​ምሩ ዘንድ እና​ንተ በኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች ሰዎች በደል በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ፋንታ ተነ​ሥ​ታ​ች​ኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እነሆም፥ የእግዚአብሔርን መዓት በእስራኤል ላይ አብዝታችሁ ትጨምሩ ዘንድ እናንተ የኃጢአተኞች ትውልድ በአባቶቻችሁ ፋንታ ቆማችኋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 32:14
19 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ የአባቶቻችሁን ሥራ የምታጸኑ ምስክሮች ናችሁ፤ እነርሱ ነቢያትን ገደሉ፤ እናንተም መቃብራቸውን ታበጃጃላችሁ።


“ ‘ልጆቻቸው ግን በእኔ ላይ ዐመፁ፤ ሰው ቢጠብቀው በሕይወት የሚኖርበትን ሥርዐቴን አልተከተሉም፤ ሕጌን ለመጠበቅ አልተጉም፤ ሰንበቴንም አረከሱ። እኔም በምድረ በዳ መዓቴን አፈስስባቸዋለሁ፤ ቍጣዬንም አወርድባቸዋለሁ ብዬ ነበር።


የምትሣለቁት በማን ላይ ነው? የምታሽሟጥጡት ማንን ነው? ምላሳችሁንስ አውጥታችሁ የምታሾፉት በማን ላይ ነው? እናንተ የዐመፀኞች ልጆች፣ የሐሰተኞች ዘር አይደላችሁምን?


እናንተ ኀጢአተኛ ሕዝብ፣ በደል የሞላበት ወገን፣ የክፉ አድራጊ ዘር፣ ምግባረ ብልሹ ልጆች ወዮላችሁ! እግዚአብሔርን ትተዋል፤ የእስራኤልን ቅዱስ አቃልለዋል፤ ጀርባቸውንም በርሱ ላይ አዙረዋል።


ተመልሰው እንደ አባቶቻቸው ከዳተኛ ሆኑ፤ እንደማያስተማምን ጠማማ ቀስት ተወላገዱ።


ከርኩስ ነገር ውስጥ ንጹሕን ማን ሊያወጣ ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም!


የቀድሞ አባቶቻችሁ ያደረጉት ይህንኑ አልነበረምን? አምላካችንስ ይህን ሁሉ ጥፋት በእኛና በዚች ከተማ ላይ ያመጣው በዚሁ በደላችን አይደለምን? አሁንም እናንተ ሰንበትን በማርከስ የባሰ መከራ በእስራኤል ላይ ታመጣላችሁ።”


ከዚያም ካህኑ ዕዝራ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ታማኞች አልነበራችሁም፤ በእስራኤል በደል ላይ በደል በመጨመር ባዕዳን ሴቶችን አገባችሁ።


እግዚአብሔርም ደስ የሚያሠኘውን መዐዛ አሸተተ፤ በልቡም እንዲህ አለ፤ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጥረታትን ዳግመኛ አላጠፋም።


አዳም፣ ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን ራሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፤ ስሙንም ሴት ብሎ ጠራው።


እርሱን ከመከተል ብትመለሱ አሁንም ይህን ሁሉ ሕዝብ በምድረ በዳ ይተወዋል፤ ለሚደርስበትም ጥፋት ምክንያቱ እናንተው ትሆናላችሁ።”


እኔ እናንተን ካወቅኋችሁ ጊዜ ጀምሮ፣ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፃችሁ ናችሁ።


“እነዚህን ምርኮኞች እዚህ ማምጣት አልነበረባችሁም፤ አለዚያ እኛ በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች እንሆናለን፤ በኀጢአታችንና በበደላችን ላይ ሌላ ልትጨምሩ ታስባላችሁን? በደላችንማ ቀድሞውኑ በዝቷል፤ ቍጣውም በእስራኤል ላይ ነውና” አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios