ማርቆስ 3:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እና አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስን አሳልፎ የሰጠውም አስቆሮታዊው ይሁዳ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሳልፎ የሰጠውንም የአስቆሮቱን ይሁዳን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሳልፎ የሰጠውንም የአስቆሮቱን ይሁዳን። |
በመናገር ላይ እያለ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ይሁዳ መጣ፤ ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ዘንድ የተላኩ ሰይፍና ዱላ የያዙ ብዙ ሰዎችም ዐብረውት ነበሩ።
ይሁን እንጂ ከእናንተ የማያምኑ አንዳንዶች አሉ።” ይህም፣ ኢየሱስ እነማን እንዳላመኑና ማን አሳልፎ እንደሚሰጠው ቀድሞውኑ ያውቅ ስለ ነበር ነው።