“ከእኔ ይልቅ እናቱን ወይም አባቱን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም።
ሉቃስ 5:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ጀልባዎቹን ወደ ምድር ካስጠጉ በኋላ፣ ሁሉን ትተው ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታንኳዎቹንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ጀልባዎቹን ወደ ምድር ካስጠጉ በኋላ ሁሉን ነገር ትተው የኢየሱስ ተከታዮች ሆኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታንኳዎቻቸውንም ወደ ምድር አወጡና ሁሉን ትተው ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታንኳዎችንም ወደ ምድር አድርሰው ሁሉን ትተው ተከተሉት። |
“ከእኔ ይልቅ እናቱን ወይም አባቱን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድድ ለእኔ ሊሆን አይገባም።
ስለ ስሜ ብሎ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን ወይም ዕርሻን የሚተው ሁሉ መቶ ዕጥፍ ይቀበላል፤ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።
ኢየሱስም ተመለከተውና ወደደው፤ “እንግዲያው አንድ ነገር ይጐድልሃል፤ ሂድና ያለህን ሁሉ ሸጠህ ለድኾች ስጥ፤ በሰማይ ሀብት ይኖርሃል፤ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ” አለው።