“ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህን ስሙ፤ “ከመጀመሪያ ጀምሮ በስውር አልተናገርሁም፤ ሲፈጸምም እኔ እዚያው ነበርሁ።” አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
ሉቃስ 4:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ግን፣ “ወደ ሌሎቹም ከተሞች ሄጄ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል መስበክ ይገባኛል፤ የተላክሁት ለዚሁ ዐላማ ነውና” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን፦ “የተላክሁት በዚሀ ምክንያት ነውና ለሌሎቹ ከተማዎችም የእግዚአብሔርን መንግሥት መልካም ዜና ማብሠር ይገባኛል፤” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ግን “እኔ የተላክሁት ለዚህ ስለ ሆነ ወደ ሌሎችም ከተሞች ሄጄ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል ማብሠር ይገባኛል፤” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ ግን፥ “ስለዚህ ተልኬአለሁና ለሌሎች ከተሞች ደግሞ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል እነግራቸው ዘንድ ይገባኛል” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱ ግን፦ ስለዚህ ተልኬአለሁና ለሌሎቹ ከተማዎች ደግሞ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እሰብክ ዘንድ ይገባኛል አላቸው። |
“ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህን ስሙ፤ “ከመጀመሪያ ጀምሮ በስውር አልተናገርሁም፤ ሲፈጸምም እኔ እዚያው ነበርሁ።” አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።
ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፣ በሕዝቡ መካከል ማንኛውንም ደዌና ሕመም እየፈወሰ በመላው ገሊላ ይዘዋወር ነበር።
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ቀባው፤ እርሱም እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ ስለ ነበረ በደረሰበት ሁሉ መልካም እያደረገ በዲያብሎስ ሥልጣን ሥር የነበሩትን ሁሉ ፈወሰ።