ሉቃስ 4:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተቀመጡበትም ተነሥተው ከከተማው አስወጡት፤ ቍልቍል ሊጥሉትም ከተማቸው ወደ ተሠራችበት ኰረብታ አፋፍ ወሰዱት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተነሥተውም ከከተማይቱ ውጭ አወጡት፤ ገፍትረውም ሊጥሉት ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ኮረብታ አፋፍ ላይ ወሰዱት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ተነሥተውም ኢየሱስን ጐትተው ከከተማ ውጪ አወጡት፤ ወደ ገደልም ገፍትረው ሊጥሉት ፈልገው ከተማቸው ወደ ተሠራችበት ኰረብታ አፋፍ ላይ ወሰዱት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያንጊዜም ተነሥተው ከከተማ ወደ ውጭ አወጡት፤ ገፍተውም ይጥሉት ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ተራራ ጫፍ ወሰዱት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይጥሉትም ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበረች ወደ ተራራው አፋፍ ወሰዱት፤ |