ሉቃስ 13:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ከፈሪሳውያን አንዳንዶች መጥተው፣ “ሄሮድስ ሊገድልህ ስለሚፈልግ ተነሥተህ ከዚህ ሂድ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ሰዓት ከፈሪሳውያን አንዳንዶች ቀርበው “ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋልና ከዚህ ውጣና ሂድ፤” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ አንዳንድ ፈሪሳውያን ወደ ኢየሱስ ቀርበው፥ “ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋልና ከዚህ ወጥተህ ሂድ” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ቀን ከፈሪሳውያን ወገን ሰዎች መጥተው፥ “ከዚህ ውጣና ሂድ፤ ሄሮድስ ሊገድልህ ይሻልና” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያን ሰዓት ከፈሪሳውያን አንዳንዱ ቀርበው፦ ሄሮድስ ሊገድልህ ይወዳልና ከዚህ ውጣና ሂድ አሉት። |
ጢባርዮስ ቄሳር በነገሠ በዐሥራ ዐምስተኛው ዓመት፣ ይኸውም ጳንጥዮስ ጲላጦስ የይሁዳ ገዥ፣ ሄሮድስ የገሊላ አራተኛው ክፍል ገዥ፣ ወንድሙ ፊልጶስ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ አራተኛው ክፍል ገዥ፣ ሊሳኒዮስም የሳቢላኒስ አራተኛው ክፍል ገዥ በነበሩበት ጊዜ፣
የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስም፣ በዚህ ጊዜ የሆነውን ነገር ሁሉ ሰምቶ በሁኔታው ተደናገረ፤ ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች ዮሐንስ ከሙታን እንደ ተነሣ ያወሩ ነበር፤