ኢያሱ 19:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ ነገድ የያዘው ርስት እጅግ ሰፊ ስለ ነበር፣ ከይሁዳ ነገድ ድርሻ ተከፍሎ ለስምዖን ነገድ በርስትነት ተሰጠ። ከዚህ የተነሣም የስምዖን ነገድ በይሁዳ ነገድ ድርሻ ርስት ሊካፈል ቻለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ ልጆች ግዛት በሆነው ክፍል ውስጥ የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፥ የይሁዳም ልጆች ድርሻ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ነገድ ድርሻ በጣም ብዙ ስለ ነበር ለስምዖን ነገድ በይሁዳ ርስት ውስጥ ድርሻ ተሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፤ የይሁዳም ልጆች ዕድል ፋንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፥ የይሁዳም ልጆች እድል ፈንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ። |
የሰበሰቡትን በጎሞር በሰፈሩ ጊዜ፣ ብዙ የሰበሰበ አላተረፈም፤ ጥቂትም የሰበሰበ አልጐደለበትም፤ እያንዳንዱ የሰበሰበው የሚያስፈልገውን ያህል ሆነ።
በርከት ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቍጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቍጥር መሠረት ይረከባል።
ደግሞም እስከ ባዕላትብኤር ወይም ኔጌብ ውስጥ እስካለው እስከ ራሞት ድረስ ባሉት ከተሞች ዙሪያ የሚገኙት መንደሮች ሁሉ ከእነዚሁ ጋራ ይጠቃለላሉ። እንግዲህ በየጐሣው የተደለደለው የስምዖን ነገድ ርስት ይህ ነበር።