ኢያሱ 19:40 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየጐሣው ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየወገኖቻቸው የተሰጠው የርስት ድርሻ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። |
“ስማቸው የተዘረዘረው ነገዶች እነዚህ ናቸው፤ “በሰሜኑ ድንበር የዳን ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የሔትሎንን መንገድ ተከትሎ እስከ ሐማት መተላለፊያ ይደርሳል። ሐጻርዔናንና ከሐማት ቀጥሎ ያለው የደማስቆ ሰሜናዊ ድንበር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ላለው ወሰኑ አንድ ክፍል ይሆናል።
በዚህ ሁኔታም ኢያሱ ተራራማውን አገር ኔጌብን፣ የምዕራቡን ቈላና የተራራውን ሸንተረሮች ጨምሮ ምድሪቱን በሙሉ ከነገሥታቷ ጋራ ያዘ። የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውም መሠረት፣ እስትንፋስ ያላቸውን ሁሉ ፈጽሞ ደመሰሰ፤ ማንንም በሕይወት አላስቀረም።
በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም። የዳን ነገድም በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስተ ድርሻውን ገና ስላልወሰደ፣ የሚሰፍርበትን የራሱን ርስት ይፈልግ ነበር።