ኤርምያስ 52:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሪብላም የባቢሎን ንጉሥ፣ የሴዴቅያስን ወንዶች ልጆች በአባታቸው ፊት ገደላቸው፤ የይሁዳንም ባለሥልጣኖች ሁሉ ገደላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች ዓይኑ እያየ ገደላቸው፥ እንዲሁም የይሁዳን አለቆች ሁሉ በሪብላ ገደላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይኸውም በሪብላ ሴዴቅያስ ራሱ በዐይኑ እያየ ወንዶች ልጆቹ ተገደሉ፤ እንዲሁም የይሁዳን ባለ ሥልጣኖች አስገደለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በፊቱ ገደላቸው፤ የይሁዳንም አለቆች ሁሉ ደግሞ በዴብላታ ገደላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በፊቱ ገደላቸው፥ የይሁዳንም አለቆች ሁሉ ደግሞ በሪብላ ገደላቸው። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “አንድ እንኳ የረባ ዘር የማይወጣለት፣ አንድ እንኳ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጥ፣ ወይም በይሁዳ የሚገዛ የማይኖረው ነውና፤ በሕይወት ዘመኑ የማይከናወንለት፣ መካን ሰው ብላችሁ መዝግቡት።”
“ ‘የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና መኳንንቱን፣ ነፍሳቸውን ለሚሹ ጠላቶቻቸው ይኸውም ለጊዜው እናንተን ከመውጋት ለተመለሱ ለባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ።
ሽማግሌውን፣ ጕልማሳውንና ልጃገረዲቱን፤ ሴቶችንና ሕፃናትን ፈጽማችሁ አጥፉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ያለበትን ሰው አትንኩ፤ ከቤተ መቅደሴም ጀምሩ።” ስለዚህ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ከነበሩት ሽማግሌዎች ጀመሩ።