በማግስቱም ታላቂቱ ልጅ ታናሺቱን፣ “እኔ ትናንትና ማታ ከአባቴ ጋራ ተኝቻለሁ፤ ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፤ አንቺም ደግሞ ከርሱ ዘንድ ገብተሽ ተኚ፤ በዚህም የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር ማትረፍ እንችላለን” አለቻት።
ኤርምያስ 5:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ዐይኖችህ እውነትን አይመለከቱምን? አንተ መታሃቸው፤ እነርሱ ግን አልተሰማቸውም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ግን አልታረሙም፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠነከሩ በንስሓ ለመመለስም አልፈለጉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ! ዐይኖችህ ለሃይማኖት አይደሉምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፤ ነገር ግን አላዘኑም፤ ቀጥቅጠሃቸውማል፤ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱም ዘንድ እንቢ አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸውማል ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፥ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፥ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ። |
በማግስቱም ታላቂቱ ልጅ ታናሺቱን፣ “እኔ ትናንትና ማታ ከአባቴ ጋራ ተኝቻለሁ፤ ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፤ አንቺም ደግሞ ከርሱ ዘንድ ገብተሽ ተኚ፤ በዚህም የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር ማትረፍ እንችላለን” አለቻት።
ይህም ሁሉ ሆኖ ኢዮርብዓም ከክፉ መንገዱ አልተመለሰም፤ ይልቁንም በኰረብታ ማምለኪያዎች ከሁሉም የሕዝብ ክፍል እንደ ገና ካህናትን ይሾም ጀመር፤ ካህን ለመሆን የሚፈልገውንም ሁሉ ለየኰረብታ ማምለኪያዎቹ ለየ።
ስለዚህም ንጉሡ ሦስተኛውን የዐምሳ አለቃ ከዐምሳ ሰዎቹ ጋራ ላከ። ይህም ሦስተኛው የዐምሳ አለቃ ወጥቶ፣ በኤልያስ ፊት በጕልበቱ ተንበርክኮ እንዲህ ሲል ለመነ፤ “አንተ የእግዚአብሔር ሰው፤ እባክህ የእኔና የእነዚህ የዐምሳዎቹ አገልጋዮችህ ነፍስ በፊትህ የከበረች ትሁን።
በፍጹም ልባቸው የሚታመኑበትን ለማበርታት የእግዚአብሔር ዐይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይመለከታሉና። የሞኝነት ሥራ ስለ ሠራህ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ጦርነት አይለይህም።”
እግዚአብሔር ሆይ፤ ክንድህ ከፍ ከፍ ብሏል፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ ለሕዝብህ ያለህን ቅናት ይዩ፤ ይፈሩም፤ ለጠላቶችህም የተዘጋጀው እሳት ይብላቸው።
ስለዚህ የሚነድድ ቍጣውን፣ የጦርነትንም መዓት አፈሰሰባቸው፤ በእሳት ነበልባል ከበባቸው፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም፤ አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን ልብ አላሉም።
“የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ ዐንገታቸውን በማደንደን ቃሌን ስላልሰሙ በዚህች ከተማና በዙሪያዋ ባሉ መንደሮች ሁሉ ላይ ላደርስ ያሰብሁትን ጥፋት ሁሉ አመጣለሁ።’ ”
ዕቅድህ ታላቅ፣ በሥራም ብርቱ ነህ፤ ዐይኖችህ የሰው ልጆችን መንገዶች ሁሉ ያያሉ፤ ለእያንዳንዱም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ።
“የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሂድ፤ ለይሁዳ ሰዎችና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ቃሌን ትጠብቁ ዘንድ ከዚህ አትማሩምን?’ ይላል እግዚአብሔር፤
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ይህ ሕዝብ አምላኩን እግዚአብሔርን ያልታዘዘ፣ ምክሩን ያልተቀበለ ወገን ነው፤ እውነት ጠፍቷል፤ ከአንደበታቸውም ሸሽቷል።
ታዲያ፣ ይህ ሕዝብ ለምን ፊቱን አዙሮ ወደ ኋላ ይሄዳል? ለምንስ ኢየሩሳሌም ዘወትር ወደ ኋላ ትመለሳለች? ተንኰልን የሙጥኝ ብለው ይዘዋል፤ ሊመለሱም ፈቃደኛ አይደሉም።
“ ‘የረከስሽው በብልግናሽ ነው፤ ቍጣዬ በአንቺ ላይ እስኪፈጸም ድረስ ከእንግዲህ ንጹሕ አትሆኚም፤ ከርኩሰትሽ ላነጻሽ ፈልጌ፣ መንጻት አልወደድሽምና።
በሙሴም ሕግ እንደ ተጻፈው፣ ይህ ሁሉ ጥፋት በእኛ ላይ ደረሰ፤ ሆኖም ከኀጢአታችን በመመለስና እውነትህን በመከተል ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ምሕረትን አልፈለግንም፤
“በግብጽ ላይ እንዳደረግሁት፣ መቅሠፍትን ላክሁባችሁ፤ ከተማረኩት ፈረሶቻችሁ ጋራ፣ ጕልማሶቻችሁን በሰይፍ ገደልሁ፤ የሰፈራችሁ ግማት አፍንጫችሁ እንዲገባ አደረግሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም” ይላል እግዚአብሔር።
“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ገለበጥኋቸው፣ አንዳንዶቻችሁን ገለበጥሁ፤ ከእሳት እንደ ተነጠቀ ትንታግ ሆናችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።
“የአትክልትና የወይን ቦታዎቻችሁን ብዙ ጊዜ መታሁ፤ በዋግና በአረማሞም አጠፋኋቸው፤ አንበጦችም የበለስና የወይራ ዛፎቻችሁን በሉ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም፤” ይላል እግዚአብሔር።
እኔም ከተማዪቱን፣ ‘በርግጥ ትፈሪኛለሽ፤ ዕርምትም ትቀበያለሽ’ አልኋት፤ ስለዚህ መኖሪያዋ አይጠፋም፤ ቅጣቴም ሁሉ በርሷ ላይ አይደርስም። እነርሱ ግን በሚያደርጉት ሁሉ፣ ክፋትንም በመፈጸም እየተጉ ሄዱ።”
ከዚህም በላይ፣ እኛ ሁላችን የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር። ታዲያ ለመናፍስት አባት እንዴት አብልጠን በመገዛት በሕይወት አንኖርም!