እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣ እንዳለው ብርሃን ነው፤ በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣ ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’
ሆሴዕ 6:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን እንወቀው፤ የበለጠ እናውቀውም ዘንድ አጥብቀን እንከተለው፤ እንደ ንጋት ብርሃን፣ በርግጥ ይገለጣል፤ ምድርን እንደሚያረሰርስ የበልግ ዝናብ፣ እንደ ክረምትም ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛም እንወቅ፤ ጌታን ለማወቅ እንትጋ፤ እንደ ንጋትም መገለጡ እርግጥ ነው፤ እንደ ዝናብ ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ በልግ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንወቀው፤ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፤ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፤ በምድርም ላይ እንደ መጀመሪያውና እንደ ኋለኛው ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንወቅ፥ እናውቀውም ዘንድ እግዚአብሔርን እንከተል፥ እንደ ወገግታም ተዘጋጅቶ እናገኘዋለን፥ እንደ ዝናብም ምድርንም እንደሚያጠጣ እንደ መጨረሻ ዝናብ ይመጣል። |
እርሱ፣ ደመና በሌለበት፣ በማለዳ ፀሓይ በምትወጣበት ጊዜ፣ እንዳለው ብርሃን ነው፤ በምድር ላይ ሣርን እንደሚያበቅለው፣ ከዝናብም በኋላ እንዳለው የብርሃን ጸዳል ነው።’
ምድርን ትጐበኛለህ፤ ታጠጣለህም፤ እጅግ ታበለጥጋታለህም። ለሰዎች እህልን ይለግሱ ዘንድ፣ የእግዚአብሔር ወንዞች ውሃን የተሞሉ ናቸው፤ አንተ እንዲህ እንዲሆን ወስነሃልና።
ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፤ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹም ልባቸውም ወደ እኔ ስለሚመለሱ፣ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
ለራሳችሁ ጽድቅን ዝሩ፤ የጽኑ ፍቅርን ፍሬ ዕጨዱ፤ ዕዳሪውንም መሬት ዕረሱ፤ እርሱም መጥቶ፣ ጽድቅን በላያችሁ እስኪያዘንብ ድረስ፣ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና።
ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፣ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
“አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ አመጣጡ ከጥንት፣ ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣ የእስራኤል ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልኛል።”
የያዕቆብ ትሩፍ፣ በብዙ አሕዛብ መካከል ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣ በሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ፣ ሰውን እንደማይጠብቅ፣ የሰውንም ልጆች ተስፋ እንደማያደርግ ሰው ይሆናል።
የበልግ ዝናብ እንዲሰጣችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ ማዕበሉን ደመና የሚያደርግ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ ለሰዎች በቂ ዝናብን፣ ለእያንዳንዱም የምድርን ተክል ይሰጣል።
የቤርያ ሰዎች ከተሰሎንቄ ሰዎች ይልቅ አስተዋዮች ስለ ነበሩ፣ “ነገሩ እንደዚህ ይሆንን?” እያሉ መጻሕፍትን በየዕለቱ በመመርመር ቃሉን በታላቅ ጕጕት ተቀብለዋል።
ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትውረድ፤ ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፣ ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ።
እንግዲያስ ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋና የንጋት ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ፣ በጨለማ ስፍራ ለሚበራ መብራት ጥንቃቄ እንደሚደረግ እናንተም ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ።
“እኔ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች እንዲመሰክር መልአኬን ለአብያተ ክርስቲያናት ልኬአለሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፣ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”