ዘፍጥረት 42:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታማኝ ሰዎች ከሆናችሁ፣ ከመካከላችሁ አንዱ እዚህ እስር ቤት ሲቈይ፣ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ትወስዱላቸዋላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታማኝ ሰዎች ከሆናችሁ፥ ከመካከላችሁ አንዱ እዚህ እስር ቤት ሲቈይ፥ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተሰቦቻችሁ እህል ትወስዱላቸዋላችሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ታማኞች ሰዎች ከሆናችሁ ከእናንተ አንዱ እዚሁ በእስር ቤት ይቈይ፤ የቀራችሁት እህሉን ይዛችሁ ወደ ተራቡት ዘመዶቻችሁ ሂዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ሰላማውያን ከሆናችሁ ከእናንተ አንዱ ወንድማችሁ በግዞት ቤት ይታሰር፤ እናንተ ግን ሂዱ፤ የሸመታችሁትን እህልም ውሰዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ የታመናችሁ ከሆናችሁ ከእናንተ አንዱ ወንድማችሁ በግዞታችሁ ቤት ይታስር እናንተ ግን ሂዱ እህሉንም ለቤታችሁ ራብ ውሰዱ |
ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለ ሄደ፣ ዮሴፍ ጐተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብጻውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላዪቱ ግብጽ ጸንቶ ነበር።
ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ።
“ከዚህ በኋላ የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው እንዲህ አለን፤ ‘ታማኝ ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው በዚህ ነው፤ ከእናንተ መካከል አንዱን ወንድማችሁን እዚህ እኔ ዘንድ ትታችሁ የተቀራችሁት ለተራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁላቸው ሂዱ።
ለአባቱም በግብጽ ምድር ከሚገኘው የተመረጠ ነገር በዐሥር አህዮች፣ እንደዚሁም ለመንገዱ ስንቅ የሚሆነው እህል፣ ዳቦና ሌላ ምግብ በዐሥር እንስት አህዮች አስጭኖ ሰደደለት።
ይህ ሕዝብ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ፣ በጕድጓድ ውስጥ የተጠመደበት፣ በወህኒ ቤት የተዘጋበት ነው፤ ተበዝብዘዋል፣ የሚያድናቸውም የለም፤ ተማርከዋል፣ “መልሷቸው” የሚልም የለም።