ዘፍጥረት 38:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳ የበኵር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳ የበኩር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ ጌታም ቀሠፈው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበረ፥ እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳም የበኵር ልጅ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ እግዚአብሔር ቀሠፈው። |
የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ። የፋሬስ ልጆች፦ ኤስሮምና ሐሙል ናቸው።
ከዚያም፣ “አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ፤ ልጇን እንዲሞት በማድረግ ተቀብላ በምታስተናግደኝ በዚህች መበለት ላይም መከራ ታመጣባታለህን?” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
የይሁዳ ወንዶች ልጆች፤ ዔር፣ አውናን፣ ሴሎም፤ እነዚህን ሦስቱን ከከነዓናዊት ሚስቱ ከሴዋ ወለደ። የበኵር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ሆነ፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።
እርሱም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ወንዶች ልጆቹን በእሳት ሠዋ፤ ሟርት፣ አስማት፣ መተትና ጥንቈላ አደረገ፤ ሙታን ጠሪዎችንና መናፍስት ሳቢዎችን ጠየቀ። ለቍጣ ያነሣሣው ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደረገ።
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል፣ እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ ይፈርዳል፤ ነገር ግን ሰው እግዚአብሔርን ቢበድል፣ ማን ይማልድለታል?” ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ስለ ፈለገ፣ ልጆቹ የአባታቸውን ተግሣጽ አልሰሙም።