ኤፌሶን 4:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ፣ እናንተም ይቅር ተባባሉ፤ እርስ በርሳችሁ ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይልቅስ እርስ በርሳችሁ ደጎችና አዛኞች ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔርም በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። |
ጻድቅ ይሞታል፤ ይህን ግን ማንም ልብ አይልም፤ ለእግዚአብሔር ያደሩ ሰዎች ይወሰዳሉ፤ ጻድቃን ከክፉ ይድኑ ዘንድ፣ መወሰዳቸውን፣ ማንም አያስተውልም።
ኢትዮጵያዊው አቢሜሌክ ኤርምያስን፣ “ይህን ያረጀ ጨርቅና ያረጀ ልብስ ገመዱ እንዳይከረክርህ በብብትህ ሥር አድርገው” አለው፤ ኤርምያስም እንዲሁ አደረገ፤
ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ መልካም አድርጉ፤ መልሳችሁ ለመቀበል ተስፋ ሳታደርጉም አበድሩ፤ በዚህም ወሮታችሁ ታላቅ ይሆናል፤ የልዑልም ልጆች ትሆናላችሁ፤ እርሱ ለማያመሰግኑና ለክፉዎች ቸር ነውና።
እናንተ ይቅር የምትሉትን ሰው እኔም ይቅር እለዋለሁ፤ በርግጥ ይቅር የምለው ነገር ካለ፣ በክርስቶስ ፊት ይቅር የምለው ስለ እናንተ ስል ነው።
በትዕግሥት የጸኑትን የተባረኩ አድርገን እንደምንቈጥር ታውቃላችሁ፤ ኢዮብ እንዴት ታግሦ እንደ ጸና ሰምታችኋል፤ ጌታም በመጨረሻ ያደረገለትን አይታችኋል። ጌታ እጅግ ርኅሩኅና መሓሪ ነው።
ኑኃሚንም ምራቷን፣ “በጎነቱን ለሕያዋንም ሆነ ለሙታን ማድረጉን ያልተወ እግዚአብሔር ይባርከው” አለቻት፤ ቀጥላም፣ “ሰውየው እኮ የሥጋ ዘመዳችን ነው፤ የመቤዠት ግዴታ ካለባቸው ዘመዶቻችን አንዱ እርሱ ነው” አለቻት።